Translation is not possible.

🚫 የፍልስጢናዊያን እልቂት ለምን ⁉️

ፍልስጢናዊያን ህፃናትና እናቶች እንዲሁም አዛውንቶች በአሜሪካና ኢስራኤል የጋራ እሳት እየነደዱ ቀሪው ዐለም እየተመለከተ ይገኛል ። !!!!! አዩዳዊያኖች የሚዘውሩት የአለም ፖለቲካ ምንነት በጉያቸው ያሉት ምእራባዊያን ምን እንደሚሉት ራሳቸው ይወቁት ።

አዩሁዶች የሚመሩት የአሜሪካ ጎንግረስና ሴኔት ኢስራኤል የምትሰራውንና የምትለውን ከማፅደቅ ያለፈ ሚና ያለው አይመስልም ። ከስሮቻቸው ያሉት ምእራባዊያንም ቢሆኑ አሜሪካና ኢስራኤል ሲዘፍኑ ከማጨብጨብ ውጪ የራሳቸው ሚና ያላቸው አይመስሉም ።

ሩስያ ዩክሬንን ስትወር ወረራ ነው ብለው ከዩክሬን ጎን ቆሙ ። ኢስራኤል ፍልስጤንን ስትወር ሽብር ነው ብለው ከኢስራኤል ጎን ቆሙ !!!!! ይህ ብቻ አይደለም ሌላውም ከኛ ጎን መቆም አለበት አሉ ። ይህ ነው ምእራቡ የሚዘውረው የዲሞክራሲ ፖለቲካ ። እነርሱ የሚሰሩት ወንጀል ፅድቅ ነው ሌላው የሚሰራው ፅድቅ ደግሞ የእነርሱን ጥቅም ካላስጠበቀ ወነጀል ነው ። ታዲያ ያሲን ኑሩ ይህን ፖለቲካ ይሁን እንዴ የእስልምና ዋናው ክፍል ነው ያለን ?‼

ከእነዚህ አካላት የሚብሱት ይህን ፖለቲካ የጠሉትና የራቁትን ዑለሞች የሚተቹት የምእራቡን ፖለቲካ እናውቀዋለን የሚሉት ኢኽዋኖች ናቸው ። እነዚህ ኢኽዋኖች አሁን በፍልስጢን እየሆነ ያለውን ነገር እንደሚሆን እያወቅን ነው ወደዚህ ጦርነት የገባነው ይላሉ ።!!!!! ሱቡሓነላህ የእነዚህ ህፃናትና እናቶች እንዲሁም አዛውንቶች እልቂት ፣ የዚህ አይነቱን የመስጂዶች ፣ ሆስፒታሎችና የትምህርት ተቋማት መንደድና መሄጃ አጥተው ሜዳ ላይ የተሰበሰቡ ሙስሊሞች በኢስራኤል የጦር ጀቶች ቦንብ መጋየት አውቀውት ይሁን ብለው ነው የገቡበት ማለት ነው ? አው ቢሉም አናምናቸውም ነገር ግን እናውቃለን የሚሉ ስለዓለሙ ፖለቲካ ጃሂሎች ናቸው እንላለን ። እንደሰው ይህን ቢያውቁ ኖሮ አይገቡበትም ነበር ። ምናልባት ከዚህ በላይም ሙስሊሞችን ቤንዚን አርከፍክፋ ማንደድ የምትፈልገው ራፊዳ ተልእኮ ለማስፈፀም መግባታቸውም ለጅህልናቸው አንዱ ማሳያ ነው ።

የፍልስጢን ኢኽዋኖች አይሁዶች የሚያደርሱት በደል ነው ለዚህ ያበቃቸው የምትሉ እህትና ወንድሞች አው እንላችኋለን ። አው የአዩሁዶች በደል ሳይሆን ለዚህ ያበቃቸው የአዩሁዶች በደል በምን መልኩ መከላከል አለብን በሚለው የነብዩ ሸሪዓ ላይ ጃሂል መሆናቸው ነው ለዚህ ያበቃቸው ።

አዩሁዶች ከፍልስጢናዊያን በፊት በነብዩ ላይ ከዚህ በላይ በደል አድርሰዋል ። ሙሽሪኩል ዐረብም እንደዚሁ ነገር ግን የአላህ መልእክተኛ እንዴት ነበር ያን ክስተት ያስተናገዱት ምን አይነት አፀፌታ ነበር የሰጡት ይህ ነው የነብዩ ተከታዮች ሞዴል ። ይህነው ካታሎጋቸው ። ይህ ነው ማኑዋላቸው ። በዛ መስመር ሲሄዱ አሸናፊ ይሆናሉ ከዛ መስመር ሲወጡ ይሸነፋሉ ።

የፍልስጢን ጦርነት ኢስራኤልና አሜሪካ ከእንጀራ ልጆቻቸው ጋር ፍልስጢንን አፈራርሶ ህዝቧን ጨርሶ ሜዳ አድርጎ ለእስራኤል ለመስጠት በአንድ በኩል በሌላ በኩል ደግሞ ኢራን በስውር ሀማስን እየመራች ከተሳካላት ኢስራኤል ሲሸነፍ ፍልስጢንን ምድርዋን ሳይሆን ህዝቧን ራፊድይ በማድረግ ህዝቡንም ምድሩንም መቆጣጠር ካልሆነ ከእስራኤል ሱንይ የምትላቸውን እንዲጠፉ በማድረግ የእጅ መንሻ ለመቀበል አላማ አድርገው የሚንቀሳቀሱበት ጦርነት መሆኑ አመላካች ነጥቦች እየታዩ ነው ።

ኢኽዋንዮቹ የሓማስ መሪዎች ይህን እያወቁ ነው እዚህ ጦርነት ውስጥ የገቡት ብሎ ለመቀበል ውጤታቸው ምንድነው የሚለው ጥያቄ መልስ ማጣቱ ይከለክላል ። የዚህ ሁሉ የፖለቲካ ድራማ መጫወቻው የፍሊስጢን ምድርና የህፃናትና አሮጊቶች እንዲሁም አዛውንቶች ጀናዛ ነው ።

ሁሉን አዋቂና ቻይ የሆነው የደካሞች አምላክ እነዚህን አውሬዎች አዋርዶ የፍልስጢንን ምድርና ህፃናት መሸሻ ያጡ አሮጊትና አዛውንቶችን ነጃ ያውጣልን ። በዐለም ላይ ያሉ አቅም ያጡ የሙስሊሞቹን ፍልስጢናዊያን መርገፍና እልቂት ሰቆቃና መከራ እያዩ ልባቸው የሚደማና ሲቃ የሚያነቡ ደካማ ሙስሊሞችን እንባ አይቶና የሲቃ ድምፃቸውን ሰምቶ ለፍልስጢናዊያን ይድረስላቸው ። ከሱ በስተቀር መሸሻም መመለሻም የለንምና አሁንም ወደርሱ ነው የምንጮኸው ደካሙቹን የሱ ባሮች ካሉበት መከራ ያውጣልን ።

ሁላችንም አላህን እንለምን ከሱ በስተቀር መላም ይሁን ሀይል ያለው የለምና ።

ከባህሩ ተካ ፅሁፍ የተወሰደ

Send as a message
Share on my page
Share in the group