Translation is not possible.

የዐሊና ፋጡማ ሰርግ

የታላቁ ነቢይ (ዐሰወ) ተወዳጅ ልጅ ፋጡማ ለጋብቻ በደረሰች ጊዜ አቡበክር (ረዐ) ሊያገቧት ጠየቁ። ነቢዩም (ዐሰወ) በታላቅ አክብሮት እንደማይቀበሉ ነገሯቸው። ሁለተኛው ጠያቂ ዑመር (ረዐ) ነበሩ። አሁን ነቢዩ (ዐሰወ) እንደማይቀበሉ በአክብሮት ነግረው መለሷቸው። እነዚህ ሁለት ታላቅ ሰሃባዎች ልጆቻቸውን ለነቢዩ (ዐሰወ) የዳሩ ቢሆንም በነቢዩ መልስ ቅንጣት አልተከፉም ነበር። በኋላ ዐሊ ከነቢዩ (ዐሰወ) ቤት መጣና ቁጭ አለ። «ምን ሆነሃል የአቡ ጧሊብ ልጅ?» አሉት። ዝም አለ። «ፋጡማን ለጋብቻ ልትጠይቀኝ አስበህ ነው?» አሉት። አፈረና አቀርቅሮ ቀረ። «መኸር የሚሆን ምን አለህ?» አሉት። «ምንም የለኝም» አላቸው። «ጋሻህስ እሱ ቢሸጥ እኮ 400 ዲርሃም ያወጣል» አሉት። ዐሊም ጋሻውን ሸጠና መኸሩን ሰጠ። ለፋጡማም አዲስ ልብስና ጌጣጌጥ ተገዛላት። ሲጋቡ እሷ የ18 እሱ የ23 ዓመት ወጣት ነበሩ። ከዚያም የሰርጉ ቀን ታላላቆቹ ሰሃባዎች ሁሉ ተገኙ። ነገርግን የሚበላ ስላልነበረ በቴምር ሰርጉን አጅበው ዋሉ። ዐሊም በቂ የኪራይ ገንዘብ በማጣቱ ከመዲና ዳርቻ ካለች ትንሽ ጎጆ ተከራይቶ ሚስቱን ይዟት ገባ። የታላቁ ንጉስ የዓለም ፈርጡ ነቢይ (0ሰወ) ልጅ ያገባችው እንዲህ ባለ ሁኔታ ነው።

የማንኛችንም ክብር ከዐሊና ከፋጡማ አይበልጥም። ኢስላማዊ ሰርግ መሰረግ የፈለገም ነቢዩ (ዐሰወ) ልጃቸው ፋጡማን በዳሩበት ሁኔታ ይሰርግ።

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group