Translation is not possible.

ተውሂድና የውስጥ ሰላም👇

👉አላህ የፈጠራቸውን ቀናት ለተለያዩ ሙታን ወይም ከአላህ ውጭ ለሚመለኩ አካላት ከፋፍሎ የሰጠ ሰው በየቀኑ ለመደባቸው አማልክት የሚፈጽመውን አምልኮ ካላደረሰ ሁለም እነዚህ አካላት በላእ ያወርዱብኛል ወይም ይቆጡኛል እያለ ይሰጋል ከዚህም አልፎ አብዛኛውን ወቅቱን ባልተደነገገ አምልኮ በማጨናነቅ ለዱንያውም ሆነ ለአኸራው መስራት ያለበትን ስራ በተገቢው ሳይሰራ ይውላል

👉ተውሂድን(አንድና ብቸኛውን አምላክ ) የያዘ ሰው ግን ቀናቶቹን በሙሉ ለፈጠራቸው አንድ አምላክ በመስጠት በየቀኑ እሱ ያዘዛቸውን በማከናወንና ከከለከለው በመራቅ ራሱን ለአላህ በማስገዛት ከአላስፈላጊ ጭንቀት ሠላም ሆኖ ይውላል👌 ከዚህ የበለጠ ምን ሰላም አለ?

አላህ ይህንን አስመልክቶ ዩሱፍ ለእስር ቤት ጓዶቹ የተናገረውን ሲተርክልን እንዲህ ይላል👇

{ يَا صَاحِبَيِ السِّجْنِ أَأَرْبَابٌ مُّتَفَرِّقُونَ خَيْرٌ أَمِ اللَّهُ الْوَاحِدُ الْقَهَّارُ }

[ سورة يوسف : 3 )

وقال يوسف للفَتَيين اللذين معه في السجن: أعبادةُ آلهةٍ مخلوقة شتى خير أم عبادة الله الواحد القهار؟

👉እናንተ የእስር ቤት ጓዶቼ ሆይ ፍጡር የሆኑ የተለያዩ አማልክትን ማምለክ ይሻላል ወይስ አንድና አሸናፊ ከሁሉም የበላይ የሆነው አላህ?

መልሱ ግልጽ ነው

አላህ በተውሂድ ኖረው በተውሂድ ከሚሞቱ ባሮች ያርገን🤲

Send as a message
Share on my page
Share in the group