Translation is not possible.

👉   በዱዓእ ስሰታም አንሁን

    ሁሉን ቻይ የሆነው ጌታ በሚሰራው ነገር ሁሉ ጥበቡ ሙሉ ነው ። ለባሮቹ እናት ለምታጠባው ልጇ ከምታዝነው በላይ አዛኝ ነው ።

   በዚህች ምድር ላይ ብዙ ግፎች ይስተናገዳሉ ። የአላህ ጠላቶች በባሮቹ ላይ የሚያደርሱዋቸውን ግፎች እያየ መተዉ እራሱ የቻለ ረቂቅ ሚስጢር አለው ። እሱ የላካቸው ነብያቶች ሲገደሉ ፣ ለሁለት ሲከፈሉ አይቶ ማለፉ ለምን እንደሆነ የሚያውቀው እሱ ነው ።

    ማን አለብን ባዮች በሱ ደካማ ፉጡሮች ላይ የሚሰሩትን ግፍ እያየ መታገሱ እሱ ለሚያውቀው ጥበብ ነው ።

     በጥቅሉ ግን በባሕርና በየብስም ቢሆን የሚከሰተው ፈሳድ በላእና ፈተና የሚመጣው የሰው ልጆች በሚሰሩት ወንጀል መሆኑን ነግሮናል ።

    የወንጀል ተፅኖ በጠላት ላይ ድል ለመቀዳጀት እንደሚከለክል አላህ የነብዩ ተከታዮች በእሁድ ዘመቻ ቀን የደረሰባቸውን ሽንፈትና ሽሽት ከእነርሱ ውስጥ ከፊሎች ከዛ በፊት በሰሩት ወንጀል ተፅኖ መሆኑን ሲነግረን እንዲህ ይላል : –

« إِنَّ الَّذِينَ تَوَلَّوْا مِنكُمْ يَوْمَ الْتَقَى الْجَمْعَانِ إِنَّمَا اسْتَزَلَّهُمُ الشَّيْطَانُ بِبَعْضِ مَا كَسَبُوا ۖ وَلَقَدْ عَفَا اللَّهُ عَنْهُمْ ۗ إِنَّ اللَّهَ غَفُورٌ حَلِيمٌ »

                    آل عمران  ( 155 )

" እነዚያ ሁለቱ ጭፍሮች በተገናኙ ቀን ከእናንተ የሸሹት ሰዎች በዚያ በሠሩት ከፊል ምክንያት ያሳሳታቸው ሰይጣን ነው ፡፡ አላህም ከነሱ በእርግጥ ይቅር አለ፡፡ አላህ መሓሪ በቅጣት የማይቸኩል ነውና ፡ ፡ "

    ከዚህ አንቀፅ የምንረዳው የወንጀል ተፅኖ ከጠላት ፊት ለፊት በሚገናኙበት ጊዜ ጭምር ድል እንደሚከለክል ነው ። ለዚህ ነው አላህ ከወንጀል እንድንርቅ አጥብቆ የሚነግረን ።

    የአላህ መልእክተኛ በተለያዩ አስተምሮዋቸው የወንጀል አስከፊነትና በቅርቢቱም ሀገር በሚቀጥለውም ዐለም ውርደት እንደሚያሸልም ያስተማሩን ። በተለይ ወንጀሉ በአላህ ላይ ማጋራት ሲሆንና በነብዩ ዲን ላይ አዲስ ነገር መፍጠር ሲሆን ክብደቱና ውጤቱ የከፋ ይሆናል ።

     አላህ እኛን ካልነበርንበት አስገኝቶ መቁጠር የማንችለው ፀጋ ሰጥቶ ተንከባክቦ እያኖረን የሱን ስልጣን ለሌላ አሳልፈን ስንሰጥ ክብደቱን እንመልከት ። ዛሬ ከሀዲያን በሙስሊሞች ላይ በሚያደርሱት ግፍ ስናይ  እየተሰማን ያለውን ህመም እንመልከትና ባሮቹ በአላህ ላይ ከሚሰሩት ወንጀል ህመም ጋር እናነፃፅረው ። የሁለተኛው የለም ቢባል መዋሸት አይሆንም ።

     አላህ አዛኙ ጌታ በእዝነቱ ለባሮቹ አዝኖ ከሚደርስባቸው ግፍና መከራ አውጥቶ ወደርሱ እንዲመለሱ እንዲያደርጋቸው ዱዓእ እናድርግ ። እርግጠኛ ነኝ ሁላችንም ታመናል ።

    በሁነይን ዘመቻ ቀን ምድር ከመስፋቷ ጋር በሶሓቦች ላይ ከጠበበች በኋላ አላህ ድል እንደሰጣቸው ሁሉ ምድር ለጠበበችባቸው ባሮቹ ድል እንዲሰጥና ማን አለብኝ ባይን እንዲያሳፍር እንለምነው ።

    እየአንዳንዱ ክስተት አስተማሪ ነውና እኛም ከዚህ ተምረን ተውበት አድርገን ወደርሱ እንመለስ ። እኛም ዛሬ ማን አለብን ብለን የነብያትን አስተምሮ አንሰማም የተውሒድ ተጣሪዎችን ጠላት እናደርጋለን ካልን የሁለት ሀገር ውርደት ይጠብቀናል ። በመሆኑም ፊታችን ወደ ተውሒድ አዙረን አላህን በብቸኝነት ማምለክና መልእክተኛውን መከተል አምሳያ የሌለው የልቅና በር መክፈቻ ቁልፍ ነው ።

    አላህ ሙስሊሞችን ወደ ተውሒድና ወደ ነብይ መከተል መልሶ የልቅና ባልተቤት ያድርግልን ። በእዝነቱ የፍሊስጢን ህፃናትና አዛውንቶችን ከአውሬ ጠላት መንጋጋ ያውጣቸው ።

     ሁላችንም ሌላ ቢያቅተን በዱዓእ አንሰስት ።

    

Send as a message
Share on my page
Share in the group