ቀደምቶቻችንን እንተዋወቅ
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
بسم الله الرحمن الرحيم
✍ ዛሬ በ الله ፈቃድ አንድ ታላቅ አሊም ኢማም ፈቂህ የሆኑ ታላቅ ሰው እንተዋወቃለን
👉👉 ኢማም አዘሀቢይ 👈👈
✍ አቡ አብዲላህ ሸምሰዲን ሙሀመድ ኢብኑ አህመድ ኢብኑ ኡስማን አዘሀቢይ ይባላሉ
✍ ይህ ታላቅ አሊም ዲመሽቅ አካባቢ ረቢአልአኺር በቀን ሶስት በ 673 ዓ ሂ ተወለዱ
✍ አባታቸውም በወርቅ ስራ የታወቁ ሰው ነበሩ በዚህም ሰበብ እሳቸውም አዘሀቢይ የሚለው መታወቂያቸው ሆነ
✍ ኢማሙ ዘሀቢይ ገና ከልጅነታቸው በጣም ከባድ የእውቀት ጉጉት እንደነበራቸው እና በጣም መልካም ሷሊህ ሰው እንደነበሩ እና እንዲሁም በአያታቸው ቤተሰብ በኩል በሙሀዲስነት ሚታወቁ ቤተሰብ እንደነበራቸው ይነገራል
✍ ይህ ታላቅ አሊም በአስራ ስምንት አመታቸው አካባቢ ቁርአንን ሙሉ ከጨረሱ በኋላ ወደ ሀዲስ ሂፍዝ ተዘነበሉ በዚህም ሰምጠው ገብተው ሀዲስ ፍለጋ ሪህላ አደረጉ በ 693 ዓሂ ማለትም በሀያ አመታቸው ሻም ዲመሽቅ አካባቢ ከነበሩ ከተለያዩ የሀዲስ ሊቆች ሀዲስን መያዝ ጀመሩ ቀጥለው በ695 ዓሂ ማለትም በሀያ ሁለት አመታቸው ወደ ሚስር ሪህላ አድርገው ሀዲስን መያዝ እና በሂፍዝ ላይ ቀጠሉ።
✍ ከዚያም በ698 ዓ ሂ በሀያ አምስት አመታቸው ከሚስር ወደ ዲመሽቅ ከተመለሱ በኋላ የሀጅ ግዴታቸውን ለመፈፀም ሄዱ በዚህም ጊዜ አስተማሪዎቻቸው አብረዋቸው ሂደው ስለነበር ይህን ክፍተት በመጠቀም ብዙ የሆኑ ሀዲሶች ለመሀፈዝ ችለው ነበር
✍ በዚህም ዘመን ላይ ከሶስት በዘመኑ ከነበሩ ታላላቅ አኢማዎች ጋር መገናኘት እና ትስስር መፍጠር ቻሉ እነዚህም 1 ሸይኹል ኢስላም ኢብኑ ተይሚያህ «661-728» 2 ጀማሉዲን አቢ ሀጃጅ አልሙዚይ«654 -739» እና 3 ሸይኽ ቃሲም አልበርዛሊይ «665-739» ናቸው ከነሱም ጋር አብሮ በመሆን ይበልጥ የሀዲስ ፍላጎታቸው እንዲጨምር እና ወደ ኢማሙ አህመድ ኢብኑ ሀንበል መዝሀብ የመዘንበል ስሜት አደረባቸው
✍ ይህ ታላቅ አሊም እስከ 703 ዓ ሂ ማለትም 30 አመት እስኪሞላቸው ድረስ ከአንድ ሺህ በላይ መሻይኾችን አግኝተው ኢልም እንደያዙ በታሪክ ፀሀፊዎች ይነገራል ከዚህም ጊዜ በኋላ የትውልድ ቦታቸው ላይ ሁነው ተማሪዎችን ይዘው ማስተማር እንዲሁም እስከዛሬ ድረስ እየተጠቀምንባቸው ያሉትን ተወዳጅ ኪታቦቻቸውን ፅፈው ማሰራጨት እና ዲነል ኢስላምን መርዳት ጀመሩ
✍ ኢማሙ ዘሀቢይ በዚህ የትውልድ ቦታቸው እያስተማሩ በነበሩበት ጊዜ በጣም ብዙ እውቀት ፈላጊዎች ወደ ቦታቸው ይጎርፍ እንደነበር እና ትልልቅ ኡለሞችንም ለማፍራት እንደቻሉ ይነገራል ከነዚህም ታላላቅ ተማሪዎቻቸው መካከል
1 ኢማም ኢብኑ ከሲር
2 ኢማሙ ኢብኑ ረጀብ አልሀንበሊይ የሚጠቀሱ ናቸው
✍ ከኢማሙ አዘሀቢይ ትልልቅ ኪታቦች መካከል ለመጥቀስ ያክል
1 تاريخ الإسلام،
2 تذهيب تهذيب الكمال
3 المغني في الضعفاء،
4 سير أعلام النبلاء،
5 الكبائر
6 الطب النبوية
7 التجريد أسماء الصحابة
የሚሉትን ኪታቦቹ ከባህር በማንኪያ ያክል ናቸው
✍✍ በመጨረሻም ሁሉም በዚህች ዱንያ ላይ ኖሮ መጨረሻ ቀኑ ሲደርስ ጥሩም ሰራ መጥፎ ኸይር አስቀመጠም ክፋት ያቺ ቀን ማትቀር ቀጠሮ ነችና ይህም ታላቅ ኢማም በቀን 3 ለይለተል ኢስነይን በ 748 ዓ ሂ ከዚህ ሀያት ወደ ማይቀረው ጉዞ ተሸጋገሩ
رحم الله الشيخ جليل إمام الذهبي وغيره من الأئمة إسلام رحمة واسعة
ቀደምቶቻችን እንተዋወቅ👇👇👇👇
Comment has been successfully reported
The post has been successfully added to your timeline!
You have reached your limit of 100000 friends!
File size error: The file exceeds the allowed limit (9 GB) and can not be uploaded.
Your video is being processed,
We’ll let you know when it's ready to view.
It's impossible to upload the file: This file type is not supported.
We have detected adult content on the uploaded image,
therefore we have declined the uploading process.
To get a verification (tick) on the Islamic social network Umma Life, you must meet at least one of the following criteria: 1. Social network activity: Participants seeking verification must be active users of the social network. At least one useful message must be posted per day, and the message topics can be non-religious. 2. A well-known Islamic blogger or Muslim: If you are a well-known Islamic blogger or Muslim, even if your activities are not related to religious topics on the Internet, you can also apply for verification. 3. A large number of subscribers or active religious pages: If you have a lot of subscribers on social networks or you actively manage useful religious pages, this can also be a basis for getting verified. If you meet at least one of these criteria, submit an application for verification on the Islamic social network Umma Life via private message https://ummalife.com/ummalife and your account will be reviewed by the social network administration.