لا يمكن الترجمة

ፈረስት ሂጂራ ፋዉንዴሽን በኦንላየን በአንድ ቀን ዉስጥ 1 ሚሊየን ዶላር ሰበሰበ።

••••••••••••••••••••••••••••••

በትላንትናዉ እለት በአሜሪካ ዋሽንግተን ዲሲ ተቀማጭነቱን ያደረገዉ የፈርስት ሂጅራ ፋዉንዴሽን ለአዲስ መስጂድና መድረሳ መግዣ የሚዉል በአንድ ቀን ዉስጥ በኦንላየን ብቻ 1 ሚሊየን ዶላር ሰበሰቡ።

የፈረስት ሂጅራ ፋዉንዴሽን ቦርድና አባላት ባደረጉት የፈንድ ራይዚንግ እንቅስቃሴ፤ በአንድ ቀን ዉስጥ አመርቂ የሚባል ዉጤት ያስመዘገቡ ሲሆን በቀጣይም በተለያየ መልኩ የቀረዉን 2 ሚሊየን ዶላር ለመሙላት አቅዶ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል።

በዚህ ድንቅ ተግባር ላይ ለተሰባሰባችሁና ሰደቃ ለሰጣችሁ በሙሉ አሏህ(ሱ.ወ) ደረጃችሁን ከፍ ያድርገዉ።

በአጭር ጊዜ ዉስጥ እንዲህ ያለ አመርቂ ዉጤት ማስመዝገቡ ሕብረታቸዉን፣ አንድነታቸዉንና ለበጎ ተግባር መሰባሰባቸዉን በጉልህ የሚያሳይ ሲሆን ሌሎችም ጀመዓዎች በዚህ መልኩ ለጋራ አላማ እንድትቆሙ ጥቆማ እንሰጣለን።

ፈረስት ሂጂራ ፋዉንዴሽን እንኳን ደስ አላችሁ!

image
image
image
image
أرسل كرسالة
شارك على صفحتي
شارك في المجموعة