Qumuqta qilghuchi yo'q.

ልትናገር ስትፈልግ ከመናገርህ በፊት ቆም ብለህ አስተውል (አገናዝብ)!!

,,,,,,,,,,,,,, ,,,,,,,,,,,,,,,

አንዳንድ ሰዎች ማገናዘብ የሚባል ነገር የተራቆተው የሆነን ንግግር በማህበራዊ ሚዲያም ሆነ በሌሎች አጋጣሚዎች ስለ ዲንም ሆነ ግለሰቦች ጉዳይ እንዳሻቸው ይናገራሉ፣ ምን ያህል አደጋው የከፋ መሆኑን ዘንግተውት ይሆን?!

ከአቢ ሁረይራ - ረዲየላሁ ዐንሁ - ተይዞ የአላህ መልእክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል:-

“አንድ ባሪያ አንዲትን ንግግር በውስጧ ምን እንዳለባት ሳያገናዝብ ይናገራል፣ በርሷ ምክንያትም በጀሀነም ከምስራቅና ምእራብ ርቀት በላይ ይወርዳል (ይወረወራል)።” [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል]

ታላቁ ዓሊም ኢማም ኢብኑ ባዝ (ረሂመሁላህ) ይህን ሀዲስ ሲያብራሩ እንዲህ አሉ:-

“ይህ ሀዲስና ሌሎችም በዚህ ሀዲስ ትርጉም የመጡ ሀዲሶች ሁሉም የንግግርን አደገኝነት ያመላክታሉ። የሰው ልጅ በምላሱ ምክንያትም አደጋ ላይ ነው ያለው። በአንድ ሰው ላይ ግድ የሚሆነው ምላሱን ሊጠብቀው ሊታገለው ነው፣ በዚህም ከክፉ ነገር (ከሸር) ሰላም ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል። ምክንያቱም ምላስ እንቅስቃሴው በመልካም አለያም በሸር ነገር ላይ በጣም ፈጣን ነው። በመሆኑም ግዴታ የሚሆነው በነገሮች ላይ ማረጋገጥና መጠንቀቅ ነው። አንተ በዝምታ ላይ ከዘውተርክ ሰላም ላይ ነህ። ከተናገርክ ደግሞ ወይ ለአንተ ነው ወይም በአንተ ላይ ነው።” [ከሪያዱ ሷሊሂን ተዕሊቅ ሀዲስ ቁ 477] የተወሰደ

ማንኛውም ሰው እያንዳንዱ የሚናገረው ቃል ክፉም ይሁን መልካም ተመዝግቦ ነገ አላህ ፊት ቀርቦ እንደሚጠየቅበት ፈፅሞ ሊዘነጋ አይገባውም!። አላህ በተቀደሰው ቃሉ እንዲህ ብሏል:-

مَّا يَلْفِظُ مِن قَوْلٍ إِلَّا لَدَيْهِ رَقِيبٌ عَتِيدٌ

«ከቃል ምንም አይናገርም በአጠገቡ ተጠባባቂና ዝግጁ የሆኑ (መላእክት) ያሉበት ቢሆን እንጅ፡፡» ቋፍ 18

ምላስህን ጠብቃት!! ዋጋ ታስከፍልሃለች!! ተቆጥተህ አትናገር አቅጣጫ ታስትሃለች!!

አንዴ ከተናገርክ በኋላ ትቆጣጠርሃለች!

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group