Translation is not possible.

ሁሌ ሳስበው ልቤን ያደማኛል አምሮዬን ያስተኛል እንቅልፌን ይነሳኛል።

ይሄን ያክል ያልነቁት ምን አይነት እንቅልፍ ቢጥላቸው ነው።

አላሁ ተዓላ አይቷል ታሪክም መዝግቧል እኛም መስክረናል ።

እስከ አፍንጫቸው በታጠቁ የአረብ ሃገራት ተከባ

ሌት በቁሩ ቀን በሐሩሩ በድሮን በታንክ ስትደበደብ ህፃናት እንደ ቅጠል ሲረግፉ : ሴቶች አዛውንቶች በግፍ ሲገደሉ ቤታቸው ሲወድም አሜሪካ ጀርመን ጣልያንና ፈረንሳይ ለወራሪዋ ደጀን ሲሆኑ አንዳቸውም ጦራቸውን አላንቀሳቀሱም።

ለወራሪዋ የጦር ድጋፍ ወታደራዊ ቁሳቁስ የጫነ የአሜሪካ አውሮፕላን በዮርዳኖስ አየር ማረፊያ በኩል ማለፉን ታሪክ በገፁ ላይ አስፍሯል።

በ21 የአረብ ሀገራት ተከባ ከ17 ቀናት በላይ ምግብ፣ መድሀኒትና ውሃ ተቋርጦባት ዓለም የሚፈራውን ጦር እንዳርበተበተች ታሪክ ተገርሞ ጋዛ ጋዛ እያለ ስሟን እየጠራ ለፍፏል።

በአቋማቸው የፀኑ ለወራሪዋም ለረዳቶቿም ያልተንበረከኩ ፅኑዎች ፍፁም የማይሰበሩ ጀግኖች ያሉባት የሸሂዶች ምድር የጀግኖች መፍለቂያ በማለት በደማቅ ብዕሩ ከትቧቸዋል።

Send as a message
Share on my page
Share in the group