Translation is not possible.

የእስራኤል አምላክ ይሄን ያደርጋል?

በርካታ በድንዛዜ ውስጥ ያሉ ሰዎች እስራኤልን የሚጠብቅ አይተኛም አያንቀላፋም በማለት ብዙ ጥቅስ በመጥቀስ አምላክ ከእስራኤል ጋር እንደቆመ ይሄ ሁሉ ጥፋት፣ ውድመት፤ ሰቆቃ፣ ስቃይ ፈጣሪ ፈቅዶ እስራኤልን ወዶ ፍልስጤምን ጠልቶ እንደሆነ አምነው በእስራኤል ድርጊት በጣም የሚደሰቱ እና የሚኮሩ ሰዎች አይቻለሁ።

.*****

አሁን ጥያቄው እናንተ የምታመልኩት አምላክ በዚህ ይደሰታል ወይ? በህፃናት ደምን በህፃናት እንባ የሚረካ አምላክ አለው ወይ? ህፃናትን እንዲህ በማያውቁት ነገር ውስጥ አካለ ጎዶሎ እና በመንፈሳቸው የሚጨነቁ እንዲሆኑ የትኛው አምላክ ይፈቅዳል? በእርግጥ የእስራኤል አምላክ በዚህ የሚረካ ነው? መልሱን እናንተ መልሱት።

.*****

እኔ ግን እንዲህ እላለሁ ማንም ከአምላክ ፍርድ አያመልጥም። በዚህ ተራ ፖለቲካ ምክንያት ብዙ ህፃናት ዋጋ እየከፈሉ ነው። በከንቱ የህፃናት ደም እንዲፈስ ላደረጉ ሁሉ አምላክ በዘመናት መካከል ቅን ፈራጅ ስለሆነ ለሁሉም እንደ ስራው እንደሚሰጠው አምናለሁ። እኔ ግን አእምሮ እንዳለው ሰው ከነዚህ ህፃናት እና ከቤተሰባቸው ጎን እቆማለሁ።

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group