Translation is not possible.

ይህች ዓለም መንገደኞች የሚሰንቁባት ወደብ ነች። ጉዞው አንድም ወደ ጀነት አሊያም ወደ ጀሃነም ይሆናል። ስራ የማይከተለው ኢማን ባዶ ነው። ዋጋውን ሳይከፍሉ ጀነትን ለመግዛት ማሰብ ሞኝነት ነው። ጉዞው ስንፍናን አያስተናግድም። የቅፍለቱ ስንቅ ለረጅም ጉዞው ምኞትን አይሰጥም። ነፍስህ ውስጥ ያለውን የመጨረሻ አቅም ለጌታህ አሳይ!። የነብይህ ሰ.ዐ.ወ. ዐይን ባንተ ይርካ። ወላጆችህን ከጀነት ያስወጣብህን ጠላት አብግን!። ጀነት ውስጥ የነብያት ጓድ ለመሆን የሚያስከፍለውን ውድ ዋጋ ለመክፈል አታቅማማ!። ዓይንህ በእንቅልፍ እጦት ይኳል! ፈረስህን ለግልቢያ ዝግጁ አድርግ!

አንተ ጥልቅ እንቅልፍ ውስጥ ያለህ ሰው ሆይ! ዘላለማዊ ጌታህን በብቸኝነት ታመልክ ዘንድ ንቃ። ሶላት ከእንቅልፍ በላጭ ነው፣ ትጋት ከመዘናጋት እጅግ የተሻለ አይደለምን?! በርካሽ እና ተራ በገሮች መርካት ትንሽነት አይደለምን?! የለፋ የልፋቱን ዋጋ ማግኘቱ ግድ ነው። የዘራ እና የኮተኮተ አዝርዕቱን ማጨዱ አይቀሬ ነው። ጀነተል ፊርደውስ ውድ ዋጋ ትፈልጋለች። የሑረል-ዓይን ጥሎሽ መቼም ቢሆን ርካሽ ሆኖ አያውቅም።

Send as a message
Share on my page
Share in the group