Translation is not possible.

በጋራ መጾምና ዱዓ ማድረግ...

🔹አንድ አሳሳቢ ነገር ሲፈጠር ዱዓ ለማድረግ በጋራ መጾም ሸርጥ ወይም ግዴታ አይደለም።

ዘወትር ሀሙስ ቀን የሚጾም ሰው ለራሱ በጾመበት አሳሳቢ ለሆኑ ነገሮች ተጨማሪ ዱዓ ያድርግ እንጂ ለአንድ አላማ ብሎ በጋራ ተጠራርቶ ጾሞ ዱዓ ማድረግ ብዙ ችግርና መከራዎችን ያሳለፉ ደጋግ ቀደምቶቻችን ዘንድ አይታወቅም!።

🔸ለሽንፈት ከሚዳርጉ ነገሮች አንዱ ቢድዓና ወንጀል መስፋፋት ነውና በሽታችን ላይ በሽታ የሚጨምር ስራ አንስራ።

🔹በመላው ዓለም ላይ በዲናቸው ምክንያት እየተሰቃዩና እየተበደሉ ያሉ ወገኖቻችንን በሙሉ አላህ ይገላግላቸው!

ለበዳዮችም የስራቸውን ይስጣቸው!

በበደል ብዛት የቆሰሉ ልቦችንም አላህ ይፈውሳቸው።

የተበዳይ ዱዓ አይመለስምና ዱዓ እናብዛ!።

✍️ኡስታዝ አሕመድ ሸይኽ ኣደም

Send as a message
Share on my page
Share in the group