Translation is not possible.

ሰውየው ኩሬ ውስጥ ይወድቃል። ውሃው ወዲህ ወድያ ሲያጫውተው የይድረሱልኝ ጩኸት ይጮህና በአካባቢው የነበሩ ሰዎች ተሰብስበው እንደ ምንም ብለው ከውሃው አዳኑት።

ቤቱ በአቅራቢያ የነበረ አንድ ሰው እየሮጠ ሄዶ ወተት ይዞለት መጣ። ትንፋሹ ተዳክሞ የነበረው ሰውዬ ወተቱን ከጠጣ በኋላ ቲንሽ ተረጋጋ። በዚህ ጊዜ ያዳኑት ሰዎች

"እንዴት ነው ውሃው ውስጥ የወደቅከው❓" ብለው ጠየቁት።

እንዴት እንደ ወደቀ እያብራራላቸው ከኩሬው ጫፍ ላይ ቆመና

"እዚህ ጋ ቆሜ ነው ያዳለጠኝ" ብሎ እየነገራቸው ድጋሚ ውሃው ውስጥ ወደቀና ሞተ።

ሼሁ ይህንን ከተናገሩ በኋላ አስተያየታቸውን ሲያስቀምጡ………

👇

👉ይህ ሰው ከተፃፈለት ሪዝቅ ያቺ ወተት ትቀረው ነበር። እሷን ሲጠጣ ግን ዱንያ ላይ የተፃፈለት ሪዝቅ አብቅቷልና እዛው ቦታ ላይ ወድቆ ሞተ።

እናም ወዳጄ፦

በምትችለው ያህል የሪዝቅ ሰበቦች ለማስገኘት ሞክር እንጂ ሪዝቄን አጣለሁ የሚል ስጋት መቼም እንዳይገባህ። የሁሉም ራዚቅ አላህ ነው። የተፃፈላትን ሪዝቅ ሳትጨርስ የምትሞት አንዲትም ነፍስ የለችን‼️‼️

منقول

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group