Translation is not possible.

ቀደምቶቻችንን እንተዋወቅ

👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇

ኡመር ኢብኑ አብዲልአዚዝ

✍ አቡ ሀፍስ ኡመር ኢብኑ አብዲልአዚዝ ኢብኑ መርዋን ኢብኑ ሀከም

የተወለዱበት አመት 61 አመት ሂጅሪያ መዲና ላይ ሲሆን ያደጉትም በታላቁ ሶሀቢይ ኡመር ኢብኑል ኸጣብ ዘር ቤተሰብ ውስጥ ነው በእውቀት ላይ ትልቅ ትኩረት የነበራቸው ሲሆን በ26 አመታቸው ወሊድ ኢብኑ አብዲልመሊክ መዲና ላይ ኸሊፋ አደረጋቸው ከዚያም የጧኢፍም ኺላፋ ጨምረው ሂጃዝን በሙሉ ኸሊፋ የሆነው የያዙት በ30 አመታቸው ነበር: ከዚያም ሱለይማን ኢብኑ አብዲልመሊክ ከሞተ በኋላ ሙሉ በሙሉ ኺላፋነትን የያዙት በ38 አመታቸው በ99 ሂጅሪያ ነበር:

• ✍ ኡመር ኢብኑ አብዲልአዚዝ በአድል የታወቀ እና በበኒ ኡመያዎች ጊዜ የነበሩት መዟሊሞችን ሙሉ ወደ አድል እና ወደ ሀቅ የመለሰበት ያማረ የኺላፋ ዘመን ያሳለፈ ኸሊፋ ነው ለዚህም ነው አንዳንዶች አምስተኛ ኸሊፋ ቢኖር ኖሮ እሱ ይሆን ነበር ያሉት የኺላፋውም ቆይታ ሁለት አመት ከአምስት ወር ከአራት ቀን አካባቢ ብቻ ነበር ከዚያም በተመረዘ ነገር ተገድሎ በ101 ሂጅሪያ በ40 አመቱ ነበር ከዚህ ዱንያ ሀያት የተለየው:

✍ እናታቸው ኡሙ አሲም ለይላ ቢንት አሲም ኢብኑ ኡመር ኢብኑል ኸጣብ ስትሆን የእናታቸው እናት ከኡመር ጋር ትልቅ ታሪክ ያላት ሰው ነበረች እሱም

👌👌 ኡመር ወተትን በውሀ አትደባልቁ ባለበት ሰአት እናት ለልጇ ውሀ ጨምሪ ስትላት ልጅም ኡመር ከልክሏል ስትላት እናትም ኡመር አያየንም በምትላት ሰአት ይህቺ ሷሊህ ልጅም ኡመር ባያየን የኡመር ጌታ ያየናል አለቻት ይህም ነገር ኡመር በሚሰማበት ጊዜ ልጅቷን ከልጆቹ ለአንዳቸው ሊድራት ፈለገ ልጆቹንም ጠርቶ እሷን መዘወጅ ሚፈልግ ከናንተ ማነው ብሎ ጠየቃቸው ከዚያም ልጁ አሲም እኔን ብትድረኝ ብሎት ተዘወጃት ከዚያም ለአሲም ለይላ ምትባል ሴት ልጅ ወለደችለት ከዚህች ከለይላ ደግሞ ታላቁ ኸሊፋ ኡመር ኢብኑ አብዲልአዚዝ ተወለዱ:

👉 ከባለቤቶቹም በጣም ታዋቂ እና የኸሊፋ ቤተሰብ ዘር እና የኸሊፋ ባለቤት በመባል ምትታወቀው ፋጢማ ቢንት አብዲልመሊክ ነች:

✍ ኡመር ኢብኑ አብዱልአዚዝ የተመረዘ ነገር ካገኘው በኋላ እና በዚያ ህመሙ እያለ 14 ወንድ ልጆች እና 3 ሴቶች የነበሩት ሲሆን ሁሉንም ሰብስቧቸው ልጆቼ ሆይ እኔ ማወርሳችገሁ ገንዘብ ምንም የለኝም እናንተ ሷሊሆች ከሆናችሁ الله ሷሊሆችን ይወዳጃል ይረዳል ከዚያ ውጪ ከሆናችሁ ግን ገንዘብ አውርሼ ሸይጧንን በናንተ ላይ አላግዝም አላቸው: እነዚህም ሷሊህ ልጆቹ ከሱ ሞት በኋላ በጣም ሀብታም ከሚባሉት ሰዎች እንደነበሩ ይነገራል!!

በአጭሩ

ቀደምቶቻችንን እንተዋወቅ👇👇👇👇

https://t.me/+T0W5e5El1xEAy9fy

Telegram: Join Group Chat

Telegram: Join Group Chat

ይህ ቻናል በ الله ፍቃድ የታላላቅ ኡለሞች ስም እና ታሪክ እንዲሁም የተለያዪ ጠቃሚ ፋኢዳዎች ሚቀርብበት ይሆናል إن شاء الله
Send as a message
Share on my page
Share in the group