Translation is not possible.
بسم الله الرحمن الرحيم
❓❓ኢብኑል ጀውዚይ እና ኢብኑል ቀይም አልጀውዚይ ማን ናቸው? የአንድ አሊም ስም ወይስ ሁለት የተለያዩ ኡለሞች ናቸው?
👉 ብዙ ጠለበል ኢልም ላይ ያሉ ውንደሞችም ሁነው ኢብኑል ቀይም አልጀውዚይ እና ኢብኑ ጀውዚይ አንድ በማድረግ ወይም የአንዱን ለአንዱ በማድረግ ኪታቦቻቸው ያንዳቸውን በአንዳቸው ስም በመሰየም ሲጠሩ አና ሲቀላቅሉት እንመለከታለን:
👉 ለዚህም አጠር ያለ ምልከታ ስለ ሁለቱ ኡለሞች ለውጥ እና ኪታቦቻቸውም በአጭሩ ምንነታቸውን እንድናውቅ በሚል ይህን አጠር ያለ ፅሁፍ ለማዘጋጀት ወደድኩኝ ጠቃሚ ይሆናል ብዬም አስባለሁ بإذن الله تعالى
1 ኢብኑል ጀውዚይ: - ጀማሉዲን አቡልፈረጅ አብዲራህማን ኢብኑ አሊይ ኢብኑ ሙሀመድ ኢብኑ አሊይ ኢብኑ አብዲላህ አልጀውዚይ ነው:
👉 ይህም ሸይኽ ብዙ ታላላቅ ኡለሞች ስለሱ ታላቅነት የመሰከሩለት አሊም ነው ከእነርሱም ውስጥ ኢማም ኢብኑ ከሲር ኢማሙ አዘሀቢይ በጣም በእውቀት ድካ የደረሰ መካሪ ሰው እንደነበር ይናገራሉ:
👉 እንዲሁም ከታላላቅ ተማሪዎቹ ውስጥ ሸይኽ አሊም አብዱልገንይ ኢብኑ አብዱልዋሂድ አልመቅደሲይ እና ሸይኽ አብዱል ሀሊም ኢብኑ ሙሀመድ ኢብኑ አቢል ቃሲም ይጠቀሳሉ:
✍✍ ከሚታወቁ ኪታቦቹ ውስጥ
" زاد المسير في علم التفسير
صيد الخاطر "
، " المنتظم في تواريخ الأمم من العرب والعجم " ،  تلبيس إبليس " ،
" أخبار الحمقى والمغفلين"
" بحر الدموع "
👉 ይህ ታላቅ ሸይኽ አንዳንድ አስማኡ ሲፋት መስአላ ላይ ወደ አሻኢራዎች ይዘነበል እንደነበር ኡለሞች ይገልፃሉ ከእነርሱም ውስጥ ታላቁ አሊም ኢብኑ ረጀብ አልሀንበሊይ ኢማም አልመቅዲሲይ የህንን ነገር ግልፅ አድርገው ያስቀምጣሉ
እንዲሁም ከዚህ ኪታቡም. " " دفع شبه التشبيه بأكف التنزيه " በአስማኡ ሲፋት መስአላ ላይ ፋኢዳ መያዝ እንደሌለብን ያስቀምጣሉ:
👌 ይህም አሊም በ597 አመተ ሂጅሪያ ላይ እንደሞተ ይነገራል::
2 ኢብኑ አልቀይም አልጀውዚይ: - ሸምሱዲን አቡ አብዲላህ ሙሀመድ ኢብኑ አቢበክር ኢብኑ አዩብ አዙረኢይ ሲሆኑ አባታቸውም በኢልመል ፈራኢድ የታወቁ እና ዲመሽቅ በሚገኘው ጀውዚያህ መድረሳ ላይ አስተማሪ ነበሩ በዚህም ሰበብ ኢብነል ቀይም አልጀውዚያ እንደተባለ ይነገራል:
👉 ኢብኑልቀይም በብዙ የእውቀት ዘርፎች የታወቁ ታላቅ አሊም ሲሆኑ ከመሻይኾቻቸውም ውስጥ ዋናው እና ለብዙ ጊዜ ሙላዘማ ያደረጉት ከሸይኹል ኢስላም ኢብኑ ተይሚያህ ጋር ነበር:
👉 እንዲሁም ከታላላቅ ተማሪዎቻቸውም ውስጥ
ኢብኑ ረጀብ አልሀንበሊይ:  ኢብኑ አብዲልሀዲይ: ኢብኑ ከሲር ይጠቀሳሉ
✍✍ ከኢብኑል ቀይም ከታዋቂ ኪታቦች በጣም በጥቂቱ
: أعلام الموقعين عن رب العالمين ،
أحكام أهل الذمة ،
بدائع الفوائد ،
زاد المعاد في هدى خير العباد ،
حادي الأرواح إلى بلاد الأفراح
الداء والدواء
 روضة الْمُحِبِّين وَنزهةُ الْمُشْتَاقِين
عِدَةُ الصَّابرين وذخيرةُ الشَّاكرين
👌 ይህም ታላቅ አሊም አለል ጃዳ እና ቀጥ ባለ አቂዳ አህለል ሱና መስመር ላይ የነበሩ ሸይኽ እንደነበሩ ኡለሞች የመሰከሩላቸው ሲሆን የሞቱትም በ751 አመተ ሂጅሪያ ላይ ነበር
ኡለሞቻችን እና ቀደምቶቻችንን እንተዋወቅ
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://t.me/+T0W5e5El1xEAy9fy
Telegram: Join Group Chat

Telegram: Join Group Chat

ይህ ቻናል በ الله ፍቃድ የታላላቅ ኡለሞች ስም እና ታሪክ እንዲሁም የተለያዪ ጠቃሚ ፋኢዳዎች ሚቀርብበት ይሆናል إن شاء الله
Send as a message
Share on my page
Share in the group