Translation is not possible.

«አል-ሐድ (الحد) ለአሏህ ማፅደቅና የአሕሉ-ሠናህ  አቋም»

--------------------------- ክፍል-2

በአሏህ ስም እጅግ በጣም ሩሕሩህና እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው እጀምራለሁ። በዚህ ፅሁፍ ስለ አል-ሐድ ለአሏህ ማፅደቅና ያለው ትርጉም እንዲሁም የአሕሉ ሡናህ ዑለማዎች አቋም እንመለከታለን።

«አሕሉ ሡናዎች ለአሏህ "ሐድ" ወይም (ከፍጡራኑ የሚለይበት ወሰን) በማፅደቅ ላይ  የጋራ ስምምነት አላቸው። ከከፊል የአሕሉ ሡና ዑለማዎች "ሐድ" ውድቅ የሚያደርጉበት ንግግራቸው ተገኝቷል። ነገርግን በዚህ ውድቅ ማድረጋቸው የሚፈልጉበት ትክክለኛን ትርጉምን ነበር በጋራ የተስማሙበትን ነገር የሚገጥም ። ጀሕሚዮች ከ"ሐድ"  ውድቅ በማድረግ የሚፈልጉበትን አይደለም። እነሱ "ሐድ" ማፅደቅን ውድቅ የሚያደርጉት የአሏህ የበላይነት ውድቅ ለማድረግ ነው።

1ኛው). አሕሉ ሡናህ ያፀደቁት "አል-ሐድ" ትርጉሙ እንይ! አሕሉ ሡናህ ወልጀመዐህ በጋራ ተስማምተው ያፀደቁት አል-ሐድ ትርጉሙ 〖 የአሏህ ሡብሃነሁ-ወተዓላ የበላይነት ማፅደቅ ፣ ከፍጡራኑ የራቀ (የተለየ ) መሆኑን ማፅደቅ ፣ በዐርሹ ላይም የተደላደለ መሆኑን ማፅደቅ ነው። 〗ይህ ነው እንግዲህ ለአሏህ «ሐድ» (ወሰን / መለያያ) ማፅደቅ ማለት።

√ ኢማም ዑስማን አድ-ዳሪሚይ (ረሂመሁሏህ) 📚አን-ነቅድ:62 እንዲህ ብሏል «አሏህ ከሠማይ በላይ በመሆኑ ላይ የሙስሊሞችና የከሃዲያን ንግግር በጋራ ተስማምተዋል። በዚህም ላይ ወስነውታል። ጠማማው አል-መሪሢና ባልደረቦቹ ሲቀር። ለአቅመ-ተክሊፍ ያልደረሱ ህፃናት እንኳን በርግጥም በዚህ አውቀውታል። »

قال الإمام عثمان الدارمي رحمه الله تعالى في 📚نقض :62 «اتفقت كلمة من المسلمين والكافرين أن الله في السماء ، وحدوه بذلك ، إلا المريسي الضال وأصحابه، حتى الصبيان الذين لم يبلغوا الحنث قد عرفوه بذلك.»

√ እዚህ ቦታ ላይ ታላቁ ኢማም ዑስማን አድ-ዳሪሚይ ረሂመሁሏህ «ሙሥሊሞች አሏህን ከሠማይ በመሆኑ ላይ ወስነውታል (حدوه) በማለት በግልፅ አስቀምጧል። ወሐዱሁ ቢዛሊክ (وحدوه بذلك) የሚለው ይህኑኑ የሚጠቁም ነው።

(ለአሏህ ወሰን/ከፍጡራን የሚለይበት ሃድ ማፅደቅ በዚህ ፍቺ ማንም ሊቃወመው የማይገባ ነገር ነው። አሏህ በሁሉም ቦታ አለ ፣ አሏህ በቦታ የለም ከሚሉ ከሃዲ ሠዎች በስተቀር።)

2ኛው). ከፊል ዑለማዎች አል-ሐድን ከአሏህ ያራቁበት ምክንያትና ሃሳባቸው እንመልከት!ከከፊል የአሕሉ ሱናህ ዑለማዎች «አል-ሐድ»ን ውድቅ አድርገዋል። ይህ ንግግራቸው በሁለት ትርጉም የሚወሰድ ነው።

1ኛው). ከፍጡራን መካከል አንድም ነገር አሏህን አያካብብም ለማለት ነው። አሏህ ልክ በቁርኣኑ እንዳስቀመጠው! እንዲህ ብሏል:-

لَّا تُدْرِكُهُ ٱلْأَبْصَٰرُ وَهُوَ يُدْرِكُ ٱلْأَبْصَٰرَ ۖ وَهُوَ ٱللَّطِيفُ ٱلْخَبِيرُ

ዓይኖች አያገኙትም፤፡ እርሱም ዓይኖችን ያያል፡፡ እርሱም ርኅራኄው ረቂቁ ውስጠ ዐዋቂው ነው፡፡

፨ በሌላም አንቀፅ አሏህ እንዲህ ብሏል :)

وَلَا يُحِيطُونَ بِهِۦ عِلْمًۭا

« በእርሱም ዕውቀትን አያካብቡም፤ (አያውቁም)፡፡ »

2ኛው). ሁሀተኛው ሃድን ውድቅ ያደረጉበት ፍጡራን የአሏህን ሐድ በተመለከተ እውቀት የላቸውም የሚል ትርጉም ነው። የአሏህን «ሐድ» ሁኔታው (كيفية) የሚያውቀው አሏህ ብቻ ነው። ለዚህ አረዳድ አትተሚሚ እንዲህ ብሏል :-

√  አቡል-ቃሢም አት-ተይሚ አል-ኣስበሃኒ (ረሂመሁሏህ) እንዲህ ብሏል « "ለሱ ሃድ የለውም" ብሎ የሚናገር ሠው በንግግሩ የፈለገበት የፍጡራን እውቀት አሏህን አያካብብም ለማለት ከሆነ ትክክል ብሏል። "ለሱ ሃድ የለውም" የሚሉት የፈለጉበት የአሏህ እውቀት በራሱ አያካብብም ለማለት ከሆነ ግን እሱ ጠማማ ነው። ወይም ኣላማው አሏህ በዛቱ በሁሉም ቦታ ነው ለማለት ከሆነ አሁን ጠማማ ይሆናል። »

√قال أبو القاسم التيمي الأصبهاني رحمه الله : « إن كان غرض القائل بقوله "ليس له حد" لا يحيط علم الخلق به ، فهو مصيب. وإن كان غرضه بذلك : لا يحيط علم الله بنفسه ، فهو ضال. وإن كان غرضه أن الله في كل مكان بذاته ، فهو أيضا ضال. »

√ ይህ ነጥብ ቀተመለከተ «አል-ሐድ»ን ማፅደቅና ውድቅ ማድረግ ግልፅ ካደረጉ ዑለማዎች መካከል ኢማም አሕመድ ቢን ሃንበል ረሂመሁሏህ አንዱ ናቸው። አንድ ቦታ አፀደቁ ፣ በሌላ ቦታ ውድቅ አደረጉ። ይህን በተመለከተ ሼይኹል ኢሥላም ኢብኑ ተይሚያህ ረሂመሁሏህ እንዲህ ብሏል ...

« ይህ ንግግር የኢማም አቡ ዐብዲላህ አህመድ ረሂመሁሏህ ንግግር ነው። ባርያዎች አሏህን ማካበባቸው ወይም ባሕሪያቱን በወሰን መገደባቸው ወይም በሆነ ልክ አሏህን መለካታቸው ወይም አሏህን በዚህ መግለፅ መድረሳቸው ውድቅ አድርጓል። ይህም ቀድሞውኑ ለአሏህ ለራሱ ሐድ ያፀደቁበትን ንግግር የሚቃረን አይደለም። አሏህ ለራሱ ሃድ አለው። የራሱን ሃድ እሱ ነው የሚያውቀው ከሱ ውጪ ማንም አያውቀውም። ወይም እሱ ራሱን ይገልፃል። እንደዚሁ ነው የሌሎችም የሠለፍ ኡለማዎች ንግግር። ያለውን ተጨባጭ ሁኔታ ያፀድቃሉ። ስለሁኔታው የባርያዎች እውቀት ውድቅ ያደርጋሉ። »

قال الشيخ ابن تيمية رحمه الله : «فهذا الكلام من الإمام أبي عبد الله أحمد رحمه الله يبين أنه نفى أن العباد يحدون الله تعالى ، أو صفاته بحد، أو يفدرون ذلك بقدر أو أن يبلغوا إلى أن يصفوا ذلك ، وذلك لا ينافي ما تقدم من إثبات أنه في نفسه له حد يعلم هو لا يعلمه غيره أو أنه هو يصف نفسه ، وهكذا كلام سائر أئمة السلف : يثبتون الحقائق ، وينفون علم العباد بكنهها. »

፨ ከዚህ ሁሉ የምንረዳው ለአሏህ «ሐድ»ን ማፅደቅ የአሕሉ ሡና አቋም መሆኑን እና ውድቅ ያደረጉትም ያፀደቁትን ዑለማዎች ንግግር የሚቃረን አለመሆኑ አይተናል። በቀጣይ በሌላ ርዕስ እንገናኛለን።

√ ወልሐምዱሊላህ ረቢል ዐለሚን

⏩ ቴሌግራም telegram.me/aqida44

Send as a message
Share on my page
Share in the group