ይበቃል ‼
ንግድ ባንክ ላይ 20 ሺ ብር አስቀምጠህ በተለያየ ጊዜ ከATM ወጪ ብታደርገው 70 ብር ይቆርጥብሀል። የዋጋ ግሽበት ደግሞ ባስቀመጥከው ጊዜ መጠን ብዙ ይቀንስብሀል። ገንዘብህ ባንኩና ኢንፍሌሽኑ ተሻርከው እየበሉህ ነውና ንቃ‼
ባንኩ ከትንሽ እስከ ትልቅ ገንዘብ ያስቀመጡ ሙስሊሞች ገንዘብ ከወለድ ነፃ ብቻ ከ1 ቢሊየን ብር በላይ ተቀማጭ አለው። ይህንን ገንዘብ ለራሱ ኢንቨስት አድርጎ አልያም ለነጋዴዎች በማበደር ብዙ ቢሊየኖች ያተርፍበታል። ይህ አልበቃ ብሎት ነው በ ATM፣ በዝውውር በአገልግሎት ስም የሚቀፍልህ። ይበቃል!
እነሱ ጋ እንድታስቀምጥ እንጂ ብድር ወስደህ ሰርተህ እንድታድግ አያበረታቱህም፣ አያበድሩህም። በዚህ ወቅት በዋጋ ግሽበት እንደምትከስር እያወቁ እንድትቆጥብ ይጀነጅኑሀል። ከወለድ ነፃ ቅርንጫፍ የሌለበት ቦታ ላይ አንድ መስኮት ላይ አንድ ሰራተኛ ያስቀምጡልህና አገልግሎት ለማግኘት ትታሻለህ። ካሽ የለም ብለው የራስህን ገንዘብ የመጠቀም መጠን ይገድቡብሀል። አዎ ካሽ የለም እነሱ እየነገዱበት ነዋ!
ፍሬንዴ ባንኮቹ ዛሬ በሰማይ ጠቀስ ህንፃ ግንባታ የሚፎካከሩት ሙስሊሙ በነፃ በሰጣቸው ገንዘብ እንጂ ከየትም አምጥተው አይደለም። ሌላው ወለድም ይቀበላቸዋል፣ በወለድም ይበደራቸዋል።
ንቃ! ገንዘብህ እራስህ ነግድበት!
ሀቢቢ ለኪሳራ አትቆጥብ‼