Translation is not possible.

👉👉👉👉:-የወጣቶችን ጤና እያመሳቀለ ያለው መድሐኒት : *ትራማዶል*

*ትራማዶል የሚባለው የህመም ማጥፊያ መድሐኒት ያለ አግባብ በወጣቶች ኪስ ተዘውትሯል። ከስምንተኛ እስከ አስራ ሁለተኛ ክፍል ያሉ ተማሪዎች በዚህ መድሐኒት ሱስ ተለክፈዋል። መድሐኒቱ ያለ በቂ ምክንያት እና ተዘውትሮ ሲወሰድ ወደ ሱስነት ይሸጋገራል።

*አንድ የገጠመኝ ተማሪ በቀን 26 ትራማዶል ክኒን መውሰድ ደረጃ የደረሰ ነበር። በቀን 26 ማለት ለመውሰድ ቀርቶ ለመቁጠር የሚታክት ነው። ሱስ የማያደርገው የለምና እያደረገ ቆይቷል። ከዚህ ደረጃ የደረሰው በአንድ ቀን አልነበረም። በቀን አንድ ተጀምሮ ቀስ በቀስ መላመድ ስላለው የሚፈለገው የሱስ ቃና ስለማያስገኝ መጠኑን እንዲጨምር በሱስ ትዕዛዝ ሁለት፣ አራት፣ ስድስት፣.....እያለ ሀያ ስድስት ክኒን ላይ ደርሷል።

*የትራማዶል ሱስ በከፍተኛ ደረጃ እየተስፋፋ የሚገኝ አደገኛ የስነ አእምሮ ችግር ነው። ከመድሐኒት ጋር ተያይዞ የሚመጣ የስነ አእምሮ ችግር የማይነካው ማዕዘን የለም። የግለሰብ ፣የቤተሰብና የማህበረሰብ ጤና፤ ኢኮኖሚ እና ማህበራዊ መስተጋብሮችን አደጋ ላይ ይጥላል።

*ትራማዶል ከድንገተኛ  መሞት እስከ ቀጣይነት ያላቸው የጤና እክሎች ያስከትላል። በአንድ ግዜ በብዛት ከተወሰደ ለሞት ይዳርጋል። የአንጎል ንዝረት፣የኩላሊት መድከም/መባባስ፣ ለጡንቻ መቅለጥ እና ለከፋ የስነ ልቦና ችግር የሚዳርግ  ነው።

*ችግሩ ትኩረት የተሰጠው አይደለም። ምንም እንኳ በጤና ጥበቃ በኩል መድሐኒቱን ያለ ልዩ ማዘዧ እንዳይታዘዝ የሚል መመሪያ ቢነገርም ተፈፃሚነቱ ላይ ግን አጠያያቂ ነው። ከዚያ ባሻገር ሰፊ የግንዛቤ መድረክ ፈጥሮ የችግሩን አሳሳቢነትና አስከፊነት ማሳወቅ ተገቢ ነው። ትኩረት ይሰጠው።

*ኪኒኑን በመውሰድ ሱሳቸውን ማብረድ ሲሳናቸው በመርፌ መውሰድ ይጀምራሉ። ከዚህ ደረጃ ተደረሰ ማለት በችግር ላይ ሰፊ ችግር ተባዝቶ ለልብና አንጎል የጤና እክል ለሚዳርግ መጥፎ ሁኔታ ይዳርጋል። የልብ በር ኢንፌክሺን በመፍጠር ለእስትሮክ ይዳርጋል።

*እስትሮክ ወጣቶች ላይ ከሚከሰትባቸው መንስኤዎች አንዱ በደም ስር የሱስ መድሐኒት መውሰድ ጋር የተያያዘ ነው። ትራማዶልና መሰል የሱስ አምጪ መድሐኒቶችን በመርፌ መውሰድ ለእስትሮክ ያጋልጣሉ።

*ሱስ ሁሉን አቀፍ የጋራ ትብብርና ቅንጅት የሚፈልግ የአእምሮ ጤና እክል ነው።

👉:-ዶር መስፍን በኃይሉ

@HakimEthio

https://ummalife.com/Meryemhassen

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group