ZuZu ZuZu shared a
Translation is not possible.
-------#እማማዬ------
⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼
የሴቶች ልክ ኪሎ መጠን፡
የእድገት ውል የመሰልጠን፡
የትሁቶች መለያ አርማ፡
የጠንካሮች ግሩም ፊርማ፡
----------#እማ-------
ገደብ የለሽ ፍቅርሽ ነው ልቅ፡
የሶስት ሆሔ ትርጉመ-ጥልቅ፡
አምላክ ችሮሽ ግሩም ቅናት፡
ስም ተሰጠሽ ተባልሽ እናት፡
የአንች ሚስጥር ረቂቅ ናት፡
----------#እማ--------------
የቁንጂናሽ ውበት፤
በፀሀይ ብርሀን መጠኑ አይለካም፡
ስለአንች ስናገር፤
ጨረቃ ነሽ ብዬ ክብርሽን አልነካም፡
አንችን በምሳሌ፤
ለሰወች ማብራራት ፈፅሞ አይሳካም፡
-------------#እማ-------------
ግሩም አንችነትሽን፤
በምድራዊ ፀጋ በምንም አልገልፀው፡
በልቤ ብቻ ነው፤
የናትነትሽን ውለታ እምቀርፀው፡
---------#እማ----------
የገዘፍሽ የደስታ ሙዳይ፡
የኔነቴ የነፍሴ ጉዳይ፡
ፍቅርሽ ረቂቅ ነው ገዳይ፡
---------#እማ---------
የማልፈታሽ ስውር ቅኔ፡
ብርታቴ ነሽ ግሩም ወኔ፡
ሳሳሁልሽ ልክ እንደ አይኔ፡
አስፈለግሽኝ ከብሌኔ፡
እማ ፍቅሬ እማ የኔ፡
---------#እማ--------
የሰውነት ሚስጥረ ጥልቅ፡
ውስጠ ወይራ ውጨ ረቂቅ፡
የኔነት ውል መቋጠሪያ፡
የፍቅር የብስ መናኸሪያ፡
የእዝነት ጥግ መከበሪያ፡
የስኬቶች ቃል መቁጠሪያ፡
-----------#እማ----------
ደማቅ ፍካት እንደ ፀሀይ፡
የቅርብ ሩቅ እንደ ሰማይ፡
ለመሸ ቀን ውብ ጨለቃ፡
ውሸት አልባ ለደቂቃ፡
መልካምነት በአንች በቃ፡
----------#እማ----------
የተስፋ አለም የነፍስ ሀሴት፡
የፍቅር መልክ የእውነት ሴት፡
ከከፍታ መውጫ ሰበብ፡
''አሊፌ'' ነሽ የኔ ጥበብ፡
---------#እማ----------
መሰቀያ ወደ ማማ፡
አንችኮ ነሽ የኔ እማማ፡
መምህሬ ውብ አርማዬ፡
ብርታቴ ነሽ ለአላማዬ፡
ሰላም ለአንች እማማዬ፡
--------------------------------
Send as a message
Share on my page
Share in the group